የናትናብሩክ አጭር የሕይወት ታሪክ "ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።" — የዮሐንስ ወንጌል 14:27 ናትና ብሩክ (ናቲ) እ.ኤ.አ. ሰኔ 22 ቀን 1998 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ከተማ ከአባቱ ከፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ እና ከእናቱ ከወይዘሮ ፀሐይነሽ ኪዳነ ማርያም ተወለደ። ገና በሦስት ዓመት ጨቅላ ዕድሜው ሳለ፣ በቤተሰብ የሥራ ዝውውር ምክንያት ከመላው ቤተሰቡ ጋር ወደ ዋሽንግተን ዲሲ (አሜሪካ) መጣ:: የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቨርጂኒያ ግዛት ማክሊን በሚገኘው በኬንት ኤለመንተሪ ትምህርት ቤት አጠናቀቀ። በመቀጠልም መካከለኛ ደረጃ ትምህርቱን በፌርላውን በሚገኘው ባዝ ኤለመንተሪና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቆ፣ በ2017 ዓ.ም. ከኦሃዮ ግዛቱ ሬቨር ሃይ ስኩል (Revere High School) በክብርተመረቀ። ናቲ ከፍተኛ ትምህርቱን በክሊቭላንድ ኦሃዮ በሚገኘው ኩያሆጋ ኮሚኒቲ ኮሌጅ በፖለቲካ ሳይንስና ሊበራል አርትስ ዘርፍ የተከታተለ ሲሆን፣ በጄምስታውን ኖርዝ ካሮላይና በሚገኘው ጂቲሲሲ (GTCC) ኮሌጅ ደግሞ በጋዜጠኝነት ሙያ ትምህርትም: ተከታትሏል። በሁሉም ዘንድ "ናቲ" እየተባለ በፍቅርና በቁልምጫ የሚጠራው ይህ ወጣት፣ ከኮሌጅ ምረቃው በኋላ በተለያዩ አካባቢዎችና ተቋማት በአገልግሎት ዘርፍ (Service Sector) በታማኝነትናበትጋት ሰርቷል። ናቲ ልዩ ማራኪ ጠባይ የነበረውና በሰላማዊ ቀልዶቹ የሁሉንም ፊት በፈገግታ የሚሞላ ድንቅ ሰው ነበር። ከትልቅ እስከ ታናሽ፣ ከሕፃናት እስከ አዛውንት ከማንኛውም የዕድሜ ክልል ጋር በቀላሉ የመግባባትና የመቀራረብ ልዩ ተሰጥኦም ነበረው። ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለባህሏ ያለው ፍቅርና ክብርም የላቀ ነበር። ናቲ መጻሕፍትን በስስት የሚያነብ፣ በሀሳብ ክርክሮች ላይ በንቃት የሚሳተፍና የአካባቢውን እንዲሁም የዓለማችንን ሁለንተናዊ ሁነቶች በጥልቀት የሚያስተውል በሳል ወጣት ነበር። በያዘው አቋምና መርህ የሚጸና፣ እምነቱንና አመለካከቱንም ያለምንም ማመንታትና ፍርሃት መግለጽ:ይወድ:ነበር:: ማኅበራዊ ኃላፊነት የሚሰማውና ለሰው አሳቢ የነበረው ናቲ፣ በማኅበረሰብ ልማትና በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ጊዜውን ይሰጥ ነበር። ለቤተሰቡ፣ ለጓደኞቹና ለሚኖርበት ማኅበረሰብ የሚራራና ለችግራቸው የሚደርስ ደግ ሰው ነበር። ቤተሰቡን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይወድ ነበር። ለወላጆቹ፣ ለወንድምና እህቶቹ እንዲሁም ለቅርብና ርቀት ዘመዶቹ የነበረው እንክብካቤ ታላቅ ነበር። ከሰዎች አልፎ ለጎረቤት የቤት እንስሳት ጭምር የሚያዝን ሩኅሩኅ ልብ ነበረው። የኢትዮጵያዊነት ቅርሱን፣ ሕዝቧን፣ ባህሏንና ያላትን ረጅም ታሪክ ያለ ምንም ወሰን በጥልቀት ያከብርና ይወድ ነበር። ለኢትዮጵያ ያለው ተቆርቋሪነት በልቡ ውስጥ የጠለቀ ሥር የሰደደ ነበር። ዛሬ በኖርዝ ካሮላይና፣ በኦሃዮ፣ በቨርጂኒያ እና በሜሪላንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባል የሆነውን የውድ ልጃችንን ውብ ሕይወት በክብር እያሰብን፣ በድንገት:ማለፉን በታላቅ ሐዘን እንገልጳለን። ናቲ ከሰው ልጆች ጋር በነበረው ጥልቅ ትስስር ሁልጊዜም በልባችን ታትሞ ይኖራል። በእጁ የዳሰሰውና የጀመረው ማንኛውም ግንኙነት፣ ጓደኝነት፣ ታማኝነትና የቤተሰብ ፍቅር የእድሜ ልክ ማኅተም ነበረው፤ እርሱ የተሰራበት ማገርና ፈትል ይኸው እውነተኛ ፍቅር ነበርና። በዩናይትድ ስቴትስ፣ በኢትዮጵያና በመላው አለም የምትገኙ የቅርብና የሩቅ ቤተሰቦች ወዳጆች በዚህ አስቸጋሪና የፈተና ወቅት ከጎናችን ለቆማችሁ፣ የሐዘን መግለጫና መጽናኛ ለላካችሁልንና አብራችሁኝ ለሆናችሁ ሁሉ የላቀና ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን:: ሽኝት ስናደርግለት፣ ከእኛ ጋር ላሳለፈው ለእያንዳንዷ ቀን ፈጣሪን እናመሰግናለን። ናቲ፣ መቼም ቢሆን አንረሳህም፤ ሁልጊዜም በልባችን ትኖራለህ። ዳግም እስክንገናኝ ድረስ ደኅና ሰንብት:: "እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ እደግፍሃለሁ።" — የኢሳይያስ ትንቢት 41:10
Natna Brook was born in Addis Ababa, Ethiopia to his father, Prof. Brook Hailu and his mother, Tsehainesh Kidane Mariam on June 22, 1998. At a very early age of three due to a family job re-location, Natna and the whole family moved to Washington DC. He started school at Kent Elementary School in McLean, VA. He completed Middle and High School at Revere High School in Fairlawn, OH, in 2017.
Affectionately called Nati by all of his family, Nati studied political science/liberal arts at Cuyahoga Community College in Cleveland, Ohio, and journalism at Guilford Technical Community College in Jamestown, North Carolina. Since his graduation from college, he has worked in the service sector in various locations.
Nati was an avid reader, debater, and observer with a deep understanding of local and global issues. He is known for holding the line, standing up for his principles, and when necessary, expressing his views without hesitation. Nati loved going on walks and appreciating nature. His favorite activities would include reading outside while listening to the sounds of nature.
Nati was a charming person and was known for his witty jokes. Nati was a kind and compassionate person who cared for family, friends and the community he lived in. He loved his family unconditionally. He cared for his parents, siblings and the extended family deeply and always constantly checking up on them. He got along with all age groups, young and old. He loved his heritage, Ethiopia, its people, culture, long history with no limits. He cared for Ethiopia deeply.
We celebrate the life of our son, a member of the Ethiopian Community in North Carolina, Ohio, Virginia and Maryland. We mourn the loss of Nati. Nati will be remembered for his charm and magical connection with the fellow man. Whatever he touched was for keeps and for life. Friendships, loyalty, love for family was the fabric he was cut from.
He is survived by his Father, Brook Hailu Beshah, Mother, Tsehainesh Gebru and Sisters, Tegist, Fana and Semhal. Nati’s immediate and larger family in the US, UK, Netherlands, Ethiopia and all of the world mourns his loss as we say goodbye to him. The family expresses our sincere thank you for the support we got, for the condolences sent from all parts of the world, and for being with us in this difficult period. When we bid farewell we are thankful for each day he was with us. Nati we will not forget, we will always remember you. Farewell Nati until we meet again.
Please join the family in honoring Natna's memory and life.
Fear not, for I am with you; be not dismayed, for I am your God; I will strengthen you, I will help you, I will uphold you with my righteous right hand. Isaiah 41:10
Funeral service will be held Saturday, June 27, 2026 at 1:00 p.m. at Phillips Funeral Service Chapel. Interment will follow at Carolina Biblical Gardens.
Final arrangements are entrusted to Phillips Funeral Service, Inc.
Please place order for floral arrangements from Ellington's Florist and Greenhouse located at 2500 S. Main St.